Error loading page.
Try refreshing the page. If that doesn't work, there may be a network issue, and you can use our self test page to see what's preventing the page from loading.
Learn more about possible network issues or contact support for more help.
Title details for በነገር ሁሉ ማደግ by Ermias Tilahun - Wait list

በነገር ሁሉ ማደግ

ebook

"ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር።" (1ጢሞ 4:15)

"በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ"(ኤፌ 4:15)

መንፈሳዊ ሕይወት በመወለድ የሚጀምርና በማደግ የሚቀጥል ነው:: በመወለድ መጀመሩ ማደግ እንዳለበት ያሳየናል:: እድገት ደግሞ የተለያየ እቅጣጫ አለው:: "ማደግህ በነገር ሁሉ ይገለጥ" ስለሚል ማደግ የሚገባን "በነገር ሁሉ" ነው:: ማደግ አንድ ነገር ሲሆን "በነገር ሁሉ ማደግ" ደግሞ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው:: እድገታችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ያለ ወይም ሚዛኑን ያልጠበቀ መሆን የለበትም:: መጽሐፍ ቅዱስ በነገር ሁሉ ማደግ እንዳለብን ብቻ ሳይሆን በነገር ሁሉ ልናድግ የምንችልበትንም መንገድ ያሳየናል:: ማደጋችን በነገር ሁሉ እንዲሆን "ይህን አስብ" ይለናል:: ይህም የምናድገው ወደምናስበው ነገር ወይም የምናስበው ነገር የምናድግበትን ሁኔታና ፍጥነት ይወስነዋል ማለት ነው::

በእድገታችን ላይ አስተሳሰባችን ትልቅ አስተዋኦ አለው:: የምናስበውን ሳንለውጥና ሳናስተካክል ልናድግበት የማንችልበት አቅጣጫ አለ:: የምናስበው ነገር የምናድግበትን አቅጣጫ ሊያፋጥነው፣ ሊጎትተው ወይም ሊያስቆመው ይችላል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ማሰብም ሆነ ምን ማሰብ እንዳለብን ያሳየናል:: ከዚህም በተጨማሪ ማደጋችን በነገር ሁሉ እንዲሆን "ይህን አዘውትር" ይለናል:: የምናስበው ነገር ብቻ ሳይሆን የምናዘወትረው ነገር (habit) ነው የሚያሳድገን:: በሌላ አባባል አዘውትረን ወደምናስበው ነገር ነው የምናድገው:: የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ቃል መጥቶ የሚሄድ፣ ብልጭ ብሎ ድርግም የሚል ሳይሆን አዘውትረን ልናስበው የሚገባንን ቃል ነው:: ሰው የሚያዘወትረውን ነገር ነው የሚሆነው:: አንዳንድ ጊዜ ለእድገታችን እንቅፋት የሚሆነው የምናስበው ነገር ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለእድገታችን እንቅፋት የሚሆነው የምናዘወትረው ነገር ነው:: ለማደግ የምንፈልግ ሰዎች ከሆንን የምናስባቸውና የምናዘወትራቸው ነገሮች ትኩረታችንን ይሻሉ:: በዚህ መጽሃፍ ልናድግባቸው የምንችላቸው ሃሳቦች እለታዊ በሆኑ ልምምዶች ማለትም ልናዘወትራቸው በምንችላቸው መልኩ ተዘጋጅተው ቀርበዋል:: ማደጋችን በነገር ሁሉ እንዲሆን ማሰብ የሚገባንን እንድናስብና ማዘውተር የሚገባንን እንድናዘወትር ብቻ ሳይሆን ወዴት ማደግ እንዳለብንም ተነግሮናል:: "በነገር ሁሉ" የምናድገው "ወደ ክርስቶስ" ነው::

Formats

  • OverDrive Read
  • EPUB ebook

Languages

  • Amharic